
አላማና ራእይ
የፋውንዴሽናችን አላማ
በዚህ ትልቅ ትምህርት ቤት ውስጥ የሚያልፉትን የነገ ሃገር ተረካቢ ትውልድ ከሌላው አካባቢ ማህበረሰብ እንዲሁም በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ በማስቻል የሚመጣው ትውልድ ሃላፊነት የሚሰማውና ብቁ ማድረግ ነው። ይህንንም ማድረግ እንድንችል በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር ያሉ የአካባቢውን ተወላጆች እንዲሁም በትምህርት ቤቱ የተማሩ ቀደምት ተማሪዎችን በማስተባበር በትምህርት ቤቱ ውስጥ ያስፈልጋሉ ተብለው የሚታሰቡትን መሰረታዊ ፍላጎቶች በማቴሪያል መልክ መርዳትና ብሩህ ተስፋ ላላቸው ነገር ግን የአቅም ውስንነት ላለባቸው ተማሪዎችም የተለያየ ድጋፍ ማድረግ ነው።
ግብ
ትምህርት ቤቱን ከመደገፍ ባለፈ በተግባር የሚያምን ፣ ታታሪና አላማ ያለው ትውልድ መፍጠር!
የመጀመርያ ምስረታ
ፋውንዴሽናችን ሰኔ 20, 2017 አ.ም ተቋቋመ።
በ 2018/2025 የተያዘ እቅድ
የመማሪያ ቁሳቁስ ለሚያስፈልጋቸው ተማሪዎች ድጋፍ ማድረግና የዲጂታል ላይብረሪውን ኮምፒውተሮችን በመግዛት በትምህርት ቤቱ ውስጥ ባለው ቤተ-መጻሕፍት ውስጥ ራሱን የቻለ አንድ ሴክሽን ማድረግ ሲሆን የoffline አገልግሎት እንዲኖረው አስተማማኝ database መፍጠር ነው።
በቀጣይ 5 አመት የተያዘ እቅድ
ከፍተኛ ውጤት ላመጡና በትምህርት ቤቱ ውስጥ በመምህርነት ሞያ ለሚያገለግሉ መምህራን የስኮላርሽፕ እድልን ማፈላለግና የማማከር አገልግሎት፣ እንዲሁም የተጀመረውን የዲጂታል ላይብረሪ ፕላትፎርም በሃገር አቀፍ ደረጃ ተቀዳሚ የሃገር resource ማድረግ ነው።
ያሳካናቸው ግቦች
134 አጋዥ መጽሃፍትን የረዳን ሲሆን በዌብ ሳይታችንም የዲጂታል ላይብረሪ እና በአለም አቀፍ ደረጃ የሚሰጡ ነጻ የኦንላይን ትምህርቶችንና የስኮላርሽፕ እድሎችን እንዲሞክሩ በማካተት ለማህበረሰባችን አበርክተናል።
የዚህ ፋውንዴሽን መስራቾች

አቤል ቢሰጠኝ
መስራች እና የትምህርት ቤቱ ተጠሪ
"በኮን 2ኛ ደረጃ ትም/ቤት ስም የተቋቋመው ፋውንዴሽን መነሻውም መድረሻውም በትምህርት ቤቱ ላሉ ማህበረሰብ (ተማሪዎች፣ መምህራን) አቅም በፈቀደ ላጋጠሙ ችግሮች መፍትሔ በመስጠት ከጊዜው ጋር ተወዳዳሪ ማድረግ ነው!"
ኮማንደር ወንድወሰን
መስራች እና ዳታ አናሊስት
"ይህ ፋውንዴሽን የኮን 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እና ተማሪዎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ፅኑ እምነት አለኝ። የዚህ ፋውንዴሽን አካል በመሆኔም ደስተኛ ይሰማኛል።"
ሰሎሞን ይመር
መስራች እና የውጭ ግንኙነት
"በዚህ ፕሮጀክት ውስጤ ትልቅ እምነት አለው ፡ የዚህ በጎ ተግባር አካል መሆኔም በጣም ያኮራኛል።"
የመስራቾቹ መልእክት
እንደ አንድ ቡድን፣ በኮን ሃይስኩል ለሚማሩ ወንድም እህቶቻችን ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር እና አስተምሮ እዚህ ደረጃ ያደረሰንን ትምህርት ቤት ለማገዝ ያለን የጋራ ስሜት ይሄንን ስራ እንድንሰራ አነሳስቶናል። ዋና ትኩረታችን ተማሪዎችንና ማህበረሰቡን ባለን ሞያ መርዳት ሲሆን ሌሎች ወንድም እህቶቻችን ይሄንን መነሻ በማድረግ ከኛ የተሻለ ነገር ለማህበረሰቡ እንዲሰሩ አርአያ መሆን ነው። እንደ ማጠቃለያ በዚህ ፋውንዴሽን መርህ መሰረት በግልፀኝነትና በትጋት አብረን በመስራት፣ ለሁሉም ማህበረሰብ ዘላቂ የሆኑ እድሎችን መፍጠር ዋና ተግባራችን ነው።