
አላማና ግብ
የፋውንዴሽናችን አላማ
በዚህ ትልቅ ትምህርት ቤት ውስጥ የሚያልፉትን የነገ ሃገር ተረካቢ ትውልድ ከሌላው አካባቢ ማህበረሰብ እንዲሁም በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ በማስቻል የሚመጣው ትውልድ ሃላፊነት የሚሰማውና ብቁ ማድረግ ነው። ይህንንም ማድረግ እንድንችል በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር ያሉ የአካባቢውን ተወላጆች እንዲሁም በትምህርት ቤቱ የተማሩ ቀደምት ተማሪዎችን በማስተባበር በትምህርት ቤቱ ውስጥ ያስፈልጋሉ ተብለው የሚታሰቡትን መሰረታዊ ፍላጎቶች በማቴሪያል መልክ መርዳትና ብሩህ ተስፋ ላላቸው ነገር ግን የአቅም ውስንነት ላለባቸው ተማሪዎችም የተለያየ ድጋፍ ማድረግ ነው።
ግብ
ትምህርት ቤቱን ከመደገፍ ባለፈ በተግባር የሚያምን ፣ ታታሪና አላማ ያለው ትውልድ መፍጠር!
የዚህ ፋውንዴሽን መስራቾች

አቤል ቢሰጠኝ
መስራች እና የትምህርት ቤቱ ተጠሪ
"በኮን 2ኛ ደረጃ ትም/ቤት ስም የተቋቋመው ፋውንዴሽን መነሻውም መድረሻውም በትምህርት ቤቱ ላሉ ማህበረሰብ (ተማሪዎች፣ መምህራን) አቅም በፈቀደ ላጋጠሙ ችግሮች መፍትሔ በመስጠት ከጊዜው ጋር ተወዳዳሪ ማድረግ ነው!"
ኮማንደር ወንድወሰን
መስራች እና ዳታ አናሊስት
"ይህ ፋውንዴሽን የኮን 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እና ተማሪዎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ፅኑ እምነት አለኝ። የዚህ ፋውንዴሽን አካል በመሆኔም ደስታ ይሰማኛል።"
ሰሎሞን ይመር
መስራች እና የውጭ ግንኙነት
"በዚህ ፕሮጀክት ውስጤ ትልቅ እምነት አለው ፡ የዚህ በጎ ተግባር አካል መሆኔም በጣም ያኮራኛል።"
መንጥር ዘሩ
የአካባቢ ተወላጅና የፋውንዴሽኑ አባል
"አሁን ዓለም ላይ የማህበረሰብ ልማቶች የሚሰሩት በጋራ እና በትብብር ነው ። የተለያዩ ዕውቀቶች ፣ የሚሰበሰቡ ሀብቶች የሆነ ግልፅ አላማ ያለው ነገር ላይ ሲውሉ ታርጌት ይመታል ። የዚህ ዓይነት ትውልድ ላይ የሚሰሩ ስራዎች በኮሚትመንት ፣ በዕምነት ፣ በትጋት መሰራት አለባቸው ። ትልቅ ሀሳብና አላማ ይዞ በትንሽ ሰዎች ፣ በትንሺ ሀብት ተጀምሮ ተዓምረኛ ስኬት ላይ የደረሱ ድርጅቶች ብዙ ናቸው ። እንበርታ !"
የመስራቾቹ መልእክት
እንደ አንድ ቡድን፣ በኮን ሃይስኩል ለሚማሩ ወንድም እህቶቻችን ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር እና አስተምሮ እዚህ ደረጃ ያደረሰንን ትምህርት ቤት ለማገዝ ያለን የጋራ ስሜት ይሄንን ስራ እንድንሰራ አነሳስቶናል።
ዋና ትኩረታችን ተማሪዎችንና ማህበረሰቡን ባለን ሞያ መርዳት ሲሆን ሌሎች ወንድም እህቶቻችን ይሄንን መነሻ በማድረግ ከኛ የተሻለ ነገር ለማህበረሰቡ እንዲሰሩ አርአያ መሆን ነው። እንደ ማጠቃለያ በዚህ ፋውንዴሽን መርህ መሰረት በግልፀኝነትና በትጋት አብረን በመስራት፣ ለሁሉም ማህበረሰብ ዘላቂ የሆኑ እድሎችን መፍጠር ዋና ተግባራችን ነው።